የኮሮና ቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ሲመረመሩ ቫይረሱ ተገኘባቸዉ፡፡


በአሜሪካ ክታባቱን ሙሉ በሙሉ የወሰዱ ሰዎች ከሁለት ሳምንታት በኋላ ሲመረመሩ የቫይረሱ ተጠቂ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡

ሃገሪቱ የክትባቱን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ በሚል 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በሚሆኑ ክትባቱን በወሰዱ ሰዎች ላይ በድጋሚ ምርመራ አድርጋለች፡፡

ከነዚህ ዉስጥም 102 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ ታዉቋል፡፡
እነዚህ ሰዎች ቀደም ሲል የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ሙሊ በሙሉ የወሰዱ መሆናቸዉም ተረጋግጧል፡፡

ክትባቱን ወስደዉ በድጋሚ ምርመራ ቫይረሱ ከተገኘባቸዉ ሰዎች መካከልም 8ቱ በጽዕኑ ታመዉ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ቱ ደግሞ ለሞት መዳረጋቸዉን ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

የዋሽንግተን የጤና መምሪያ ባወጣዉ ሪፖርት፣የተከተቡ ሰዎችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልን ከመጠቀም ጀምሮ የትኛዉም ክትባቱን ያልወሰደ ሰዉ የሚያደረጋቸዉን የጥንቃቄ ርምጃዎች ማድረግ እንዳለባቸዉ የሚያሳይ ነዉ ብሏል፡፡

ቀደም ሲል ኖርዌይ ክትባቱን ከወሰዱ ሰዎች ዉስጥ 33 በሚሆኑት ላይ በድጋሚ ቫይረሱ እንደተገኘባቸዉ ብታስታዉቅም የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ትኩረት ሳይሰጡት መቆየታቸዉ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡-ኤቢሲ ኒዉስ

በሙሉቀን አሰፋ
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.