በማሊ 4 የተባበሩት መንግስት ድርጅት ሰላም አስከባሪ አባላት በታጣቂዎች ተገደሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳህል ክልልን ሰላም ለማስጠበቅ ካሰማራቸው ወታደሮች ውስጥ በማሊ ምድብ ከሚገኙት መካከል 4ቱ መገደላቸውን አስታውቋል።

ሰላም አስከባሪ አባላቱ የተገደሉት በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኝ ካምፕ ላይ ሰርጎ ገብ አሸባሪዎች ድንገት በከፈቱት ጥቃት ነዉ።

በጥቃቱ በቁጥር ያልተገለፁ በርካታ የሰላም ማስከባሪ አባላት መቁሰላቸውም ተነግሯል።

ጥቃቱን ያደረሰው የሽብር ቡድን በጣም የተደራጀና ከባድ መሳሪያ የታጠቀ እንደነበር ታውቋል።

የሰላም አስከባሪ አባላቱ ድንገተኛውን ጥቃት ከመመከታቸውም በላይ በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላትን መደምሰስ መቻላቸው ተገልጿል።

ቢቢሲ

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.