እገዳውን ለመጣል ያበቃቸውም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ታስቦ እንደሆነ ነው የተገለጸው።
በሁለቱም ሀገራት በኩል የኮቪድ ደንቦችን ባላገናዘበ መልኩ በአሉን ለማክበር በሚሊዮን የሚቆጥሩ ዜጎች ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ተከትሎ ነዉ እገዳዉ የተጣለዉ ተብሏል።
አሁንም በአዉሮፓ ሀገራት ገና የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙሉ በሙሉ ተደራሽ አለመሆኑ ይነገራል።
የቫይረሱ ስርጭት ግን በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ ሀገራቱ እንቅስቃሴዎችን ዝግ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በዚህም ፈረንሳይ በአንዳንድ አካባዎች ላይ ለ3ኛ ጊዜ ሀገራዊ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ተሰምቷል።
አሁን በፈረንሳይ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው እንደሚገኙም ሮይተርስ ዘግቧል።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም











