መዘናጋት አሁንም ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለን ነዉ!

የኮሮና ቫይረስ እያደረሰ ያለዉ ተጽዕኖ እየበረታ ይገኛል፡፡

የጤና ሚንስቴር መረጃ እንደሚያመለክተዉ በትናንትናዉ እለት ብቻ 37 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

ይህ ቁጥር እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት በሃገራችን በአንድ ቀን በርካታ ወገኖቻችን ህይወታቸዉን ያጡበት ከፍተኛዉ ቁጥር ነዉ፡፡

ለ9 ሺህ 37 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎ 2 ሺህ 138 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸዉም ተረጋግጧል፡፡ 862 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክፍል ዉስጥ ይገኛሉ ነዉ የተባለዉ፡፡

በዚህም የተጠቂዎች ቁጥር 217 ሺህ 327 የደረሰ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 3 ሺህ መድረሱን የጤና ሚንስቴር አስታዉቋል፡፡

የጤና ሚንስቴር ከዚህ ቀደም አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያዎች እጥረት እንዳለ መግለጹ የሚታወስ ነዉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *