ሱዳን በዳርፉር 40 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች፡፡

በትላንትናው እለት በምዕራባዊ የዳርፉር ግዛት 40 ሰዎች ለህልፈት ህይወት መዳረጋቸውን ተከትሎ ሱዳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ በግዛቲቱ አል ጀኒና ከተማ ውስጥ በዓረብ እና መሳሊጥ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

እንዲሁም ከ 50 በላይ በሚሆኑት ላይ የመቁሰል አዳጋ እንደደረሰባቸው ያመላከተው ድርጅቱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡

ባሳለፍነው ጥር ወር በአካባቢው በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 129 ሰዎች ለህልፈተ ህይዎት ሲዳረጉ፤ ከ108 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

ሱዳን ትሪቡን

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *