አፍሪካ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር 12 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ፡፡

የአለም ባንክ ባቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው የአፍሪካ ሀገራት በቂ የሆነ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማግኘት 12 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል ብሏል፡፡

ባንኩና አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የቡድን 7 አባል ሀገራት በአፍሪካም ሆነ በሌሎች የአለም ክፍሎች ለሚገኙ ደሃ ሀገራት ያለባቸውን እዳ እንዲሰርዙላቸው ይህ ካልሆነም የመክፈያ ጊዜውን እንዲያራዝሙላቸውም ጠይቀዋል፡፡

በአለም ባንክና በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አዘጋጅነት በአለም ዙሪያ፤ ክትባቱ ተደራሽ የሚሆንበት፣የድሃ ሀገራት የብድር ጫናና አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ምክክር እያደረጉ ነዉ፡፡

ቢቢሲ

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *