ፑቲን ለተጨማሪ ሁለት የስልጣን ዘመናት በፕሬዝደንትነት መቆየት የሚያስችል ሕግን ፈርመዋል፡፡

ህጉ የ 68 ዓመቱ የሩሲያ ፕሬዝዳንት እስከ 2036 ድረስ በስልጣን የመቆየት እድልን ይፈቅድላቸዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እስከ ፈረንጆቹ 2036 ድረስ ለሁለት ተጨማሪ ስድስት ዓመታት የሥልጣን ጊዜያቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችለውን ሕግ በመጨረሻም በፊርማ አረጋግጠዋል ፡፡

ቀደም ሲልም ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ የቆዩት የ 68 ዓመቱ የሩሲያ ፕሬዝደንት አሁንም በቤተመንግስቱ መቆየት የሚያስችል ህግን ትላንት ሰኞ ነው በፊርማቸው ያረጋገጡት፡፡

ከሶቪዬት አምባገነን መሪ ጆሴፍ እስታሊን በኃላ ፑቲን በክሬምሊን ቤተመንግስት ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆዩ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡

የአሁኑ የስድስት ዓመት ስልጣናቸው በ2024 ይጠናቀቃል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ቀደም ብለው በድጋሚ በምርጫ ለመወዳደር የሚያስችላቸውን የህገመንግስት ማሻሻያ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

አልጀዚራ

በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.