ለኃይማኖት አባቶች የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዛሬ እየተሰጠ ነዉ፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳለዉ ክትባቱን ለሁሉም የኃይማኖት አባቶች ለመስጠት ፕሮግራም ተይዟል፡፡

በዚህም መሰረት ዛሬ ረፋድ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፓትርያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ ክትባቱን ወስደዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ የኢትዮጵያ እስልምና ኃይማኖት ጉዳዮች ምክር ቤት ኃላፊ ተቀዳሚ ሀጂ ሙፍቲ ፣የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ካርዲናል ብጹህ አቡነ ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል እና የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን መሪ ክትባቱን ያገኛሉ ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *