ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ከ1 ሺህ በላይ ተረጅዎችን እየተንከባከብኩ ቢሆንም በቦታ ችግር ተማርሪያለሁ ብሏል፡፡

ችግሬን ለከተማ አስተዳደሩ በተደጋጋሚ ባሳዉቅም ምላሽ ላገኝ አልቻልኩም ብሏል ማህበሩ፡፡

ከዚህ ቀደም በ160 ሺህ ብር እየከፈለ ይጠቀምበት የነበረውን ቦታ ሊለቅ መሆኑን የገለጸዉ ማህበሩ ምክንያቱ ደግሞ ቦታዉ በባለቤቶች በመፈለጉ መሆኑን ገልጿል፡፡

በዚህም ለ 21 ዓመታት 160 ሺ ብር ኪራይ እየከፈለ ይጠቀምበት የነበረውን ቦታ ከ ሰኔ 30 ጀምሮ እንደሚለቅ ማህበሩ ገልጿል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሙዳይ የቦታ ችግርን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን 50 ሺህ ካሬ ሜትር እንዲሰዉ መጠየቁን አንስቶ ነገር ግን ምላሽ አልተሰጠንም ብለዋል::

የሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ፣ በእቅድ ደረጃ ከ ሰኔ 30 በኃላ እንዴት እንደምንቀጥል ከ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ቢሮ ጋር ዉይይት እየተደረገ ነው፤ ውሳኔ ላይ ግን ገና አልተደረሰም ብለዋል።

በሌላ በኩል ማህበሩ ከሚያዚያ 3 እስከ ሚያዚ 10 ለአንድ ሳምንት ያህል የፍቅር ሳምንት በሚል መርሃ ግብር ያከናዉናል ተብሏል።

በመርሃ ግብሩ ላይ መጪው ጊዜ የፋሲካ በዓል እየተቃረበ በመሆኑ፣ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በአሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ታስቦ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል።

በእለቱም ድጋፍ ለሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች ማንኛውም ግለሰብና ተቋም በእውቀትና በገንዘብ የአቅሙን ያህል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪም ቀርቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *