ኒውዝላንድ ከህንድ የሚመጡ ተጓዦች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገደች፡፡

ኒውዝላንድ ይህን እርምጃ የወሰደችዉ በህንድ ተባሶ በቀጠለዉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንይት ነዉ፡፡

በሀገሪቱ ድንበር ላይ 23 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉን የገለጸችዉ ሃገሪቱ ከነዚህ ውስጥ 17ቱ ከህንድ የገቡ ናቸው ብላለች፡፡

በተከታታይ ለሁለት ሳምንት በደቡብ እስያ ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት መታየቱ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የኒውዝላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄሲንዳ አርድነር ለተወሰነ ጊዜ ከህንድ የሚገቡ ተጓዦች ላይ ክልከላ አድርገናል ብለዋል፡፡

አጽንኦት መስጠት የምፈልገው ይህ ውሳኔ ከፍተኛ ተጋላጭነትን እንዴት መከላከል እንችላለን ብለን የወሰንነው ዉሳኔ እንጂ አንድን ሃገር ብቻ ያማከለ አይደለም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ፡፡

በህንድ 12 ነጥብ 8 ሚሊየን የኮሮና ኬዝ የተመዘገበ ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃም ከአሜሪካና ብራዚል ቀጥሎ በ3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

አልጀዚራ

በመቅደላዊት ደረጀ
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.