ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን በምስራቅ ሪጅን በይፋ አስጀምሯል፡፡

አገልግሎቱ በ7 ከተሞች ይፋ የተደረገ ሲሆን ጅግጅጋ፣ ጎዴ፣ ፊቅ፣ ደገሃቡር፣ ቀብሪ በያህ፣ ዋርዴር እና ቀብሪ ደሀር የ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት የተጀመረባቸው ከተሞች መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ ወቅቱና አካባቢዉ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ አስቸጋሪ ቢሆነብም ይህን ተቋቁሞ ኩባያዉ የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረጉን ተናግረዋ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሪጅኑ የኔትወርክ ሽፋን እና አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ የኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *