የማይናማር የእንግሊዝ መልዕክተኛ ወታደራዊ አታሺ ኤምባሲውን ‘ተቆጣጥረውታል’ አሉ

በለንደን የሚገኘው የማይናማር አምባሳደር ኤምባሲው ተዘግቶ እንደተቆለፈ ተናግረዋል፡፡

ካያው ዝዋር ሚን እንዳሉት ሠራተኞች ከማያንማር የመጡ ወታደራዊ አታሺዎች ሕንፃውን ለቀው እንዲወጡ ማድረጋቸውን እና ከአሁን በኋላ የአገሪቱ ተወካይ እንዳልሆኑ ነግረዋቸዋል ብለዋል፡፡

ለሮይተርስ እኔም ቢሆን ተዘግቶብኝ ነበር ነው ያሉት፡፡

የማያንማር ጦር ሀይል የካቲት 1 ቀን ባደረገው መፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን መቁጣጠሩ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የተነሳም ለሳምንታት ከፍተኛ የተባለ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄደዋል፡፡

ከ500 በላይ ህጻናትን ጨምሮ ተገድለዋል፡፡

ካው ዝዋር ሚን ከስልጣን የተወገዱት መሪ አውን ሳን ሱ ኪ እንዲለቀቁም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *