የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንዳለዉ በከተማዋ ትናንት ሌሊት በአራት የተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡
በእሳት አደጋዉ 7 ሚሊዮን 550 ሺህ ብር ግምት ያለው ንብረት እንደወደመ ነዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያስታወቀዉ፡፡
የእሳት አደጋው የተከሰተውም በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች መሆኑን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ተናግረዋል፡፡
በአደጋዉም የአባወራ ቤቶች፣መጋዘኖች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 “መለስ ፋውንዴሽን” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 8 የተከሰተው አደጋ አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑን ለኢዜአ የገለጹት አቶ ጉልላት፣
በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 6 የተከሰተውን አደጋ ገና ፖሊስ እያጣራው መሆኑን ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ሁለት ወረዳዎች የደረሰው አደጋ መንስኤ ደግሞ አንደኛው የኤሌክትሪክ ኮንታክት እና ሌላኛው እስካሁን ምክንያቱ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 01 ቀን 2013 ዓ.ም











