የህዳሴዉ ግድብን በተመለከተ ወታደራዊ አማራጭ ቦታ የለዉም—-ሱዳን!

በህዳሴዉ ግድብ ላይ ያሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉት በሚደረጉ ፖለቲካዊ ዉይይቶች መሆኑን ሱዳን እንደምታምን የሃገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ተናግረዋል፡፡

ሚንስትሯ መርያም አል-ሳድቅ አል-ማህዲ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉት በፖለቲካዊ ጉዳዮች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ዉጭ ግን ወታደራዊ አማራጭ ምንም ቦታ እንደሌለዉ ተናግረዋል፡፡

ሚንስትሯ በኳታር ዶሃ ጉብኝት እያደረጉ በነበሩበት ወቅት፣ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ግብጽና ሱዳን ጥቅማችንን ይጎዳል የሚል ስጋት እንዳለባቸዉ ያነሳሉ፤ ወታደራዊ አማራጮች ሊኖሩ ይችላሉ ወይ? በሚል ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ሚንስትሯ ሲመልሱ፣ በፍጹም ወታደራዊ አማራጭ ቦታ የለዉም፤ መፍትሄ ሊሆንም አይችልም ብለዋል፡፡

ከዚህ ይልቅ የዓለም አቀፋ ማህበረሰብ በተለይም ደግሞ የአፍሪካ ሀገራት በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ለመፍትሄዉ እንዲተጉ እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል ሚንስትሯል፡፡

ቀደም ሲል የሱዳን የዉሃና መስኖ ሚንስቴር ሱዳን ጉዳዩን እስከ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታዉ ምክር ቤት ድረስ ልትወስደዉ እንደምትችል ተናግረዉ እንደነበር ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

ይሁንና የሃገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚነስትር አሁን ላይ ጉዳዩን ጎረቤቶቻችን የአፍሪካ ሀገራት ትኩረት እንዲሰጡት እናደርጋለን ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ፍትሃዊ የሆነ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ዉይይቶችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ስትገልጽ ቆይታለች፡፡
አሁንም በዚህ አቋሟ እንደጸናች ናት፡፡

የሁለተኛዉ ዙር የዉሃ ሙሌትንም ለማከናወን ምንም የሚያግዳት ሃይል እንደሌለ መግለጿም የሚታወስ ነዉ፡፡
ኤ ኤፍ ፒ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.