የአፍሪካ ህብረት ከህንድ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማስገባት የያዘውን እቅድ ሰረዘ።

ህብረቱ ከህንዱ ክትባት አቅራቢ ተቋም ሴረም ኢንስቲትዩት ክትባቶችን ተቀብሎ ወደ አፍሪካ ለማስገባት የጀመረውን እንቅስቀሴ ማቋረጡን ነው ያስታወቀው።

ለማቋረጡ እንደ ምክንያት የጠቀሰዉም የሚያስፈልገኝን ያህል የክትባት አቅርቦት ኢንስቲትዩቱ ባለመኖሩ ነዉ ብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ክትባቶችን ከህንድ ወደ አፍሪካ ለማስመጣት በህንድ በኩል የማይመች አሰራር በመፈጠሩ ነው ብሏል ህብረቱ።

በመሆኑም የአፍሪካ ህብረት ከዚህ በፊት 400 ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ለማስገባት ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጋር ውል መፈፀሙን ገልጿል።

በመሆኑም ክትባቶችን ከህንድ ለማስመጣት የያዘዉን እቅድ የሰረዘዉ ከአቅርቦትና ቀልጣፋ አሰራር ጋር በተያያዙ ችግሮች እንጂ ክትባቱ የደም መርጋትን ያመጣል በሚል እንዳልሆነ ህብረቱ አስታውቋል።

ሮይተርስ

በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.