በብራዚል 19 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል ተባለ፡፡

በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተጽዕኖን ተከትሎ በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የተካሄደው ጥናት እንዳረጋገጠው፣ በአሁኑ ወቅት በብራዚል 19 ሚሊዮን ዜጎች ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ መዳረጋቸዉን ይፋ አድርጓል።

እንዲሁም ብራዚል ካላት ህዝብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ማለትም 117 ሚሊዮን የሚሆኑት ዜጎቿ ደግሞ ከባድ የረሃብ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ነው ጥናቱ ያመላከተው።

በሃገሪቱ ከሰሞኑ በአንድ ቀን ብቻ ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

እስካሁን ድረስ ከ350 ሺህ በላይ ዜጎቿን በኮሮና ያጣችዉ ብራዚል በዓለም አቀፍ ደረጃ ቫይረሱ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካደረሰባቸዉ ሀገራት መካከል ከአሜሪካ ቀጥላ በ2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

በመሆኑም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በጥናታቸው እንደጠቆሙት ቫይረሱ ይዞት በመጣው ተፅእኖ በሀገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት የስራ አጥ ቁጥሩ እንዲጨምር አድርጓል።

ይህ ደግሞ በመሰረታዊ የምግብ አቅርቦቶች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ዋጋው እንዲንር በማድረጉ ዜጎች እንዲራቡ አድርጓቸዋል ነው ያሉት።

አልጃዚራ

በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.