ኳታር በመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት ልትሰጥ ነዉ፡፡

ሃገሪቱ በዓለምአቀፍ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ከ3.6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነዉ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ልትከትብ መሆኑን ያስታወቀችዉ፡፡

በኳታር የሚገኘው ”ሬድ ክረሰንት” የተሰኘው መርጃ ድርጅት፣ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር በአለም ዙሪያ በስራቸው ለኮቪድ ተጋላጭ ለሆኑና በመጠለያ ጣብያዎች ለሚገኙ ሰዎች ነዉ ክትባቱን የሚሰጠዉ፡፡

ክትባቱን ያገኛሉ የተባሉ ስደተኞችም 3 ሚሊዮን 650 ሺህ የሚሆኑ ናቸዉ ተብሏል፡፡

ከነዚህ ዜጎች በተጨማሪ ለእድሜ ባለጸጎች፣ ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው ሰዎች እንዲሁም የህክምናና የሰብዓዊ አገልግሎት ለሚሰጡ ባለሙያዎችም ክትባቱ እንደሚሰጥ ድርጅቱ አስታውቋል።

በዓለም ከ20 በላይ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ በተለይም በአፍጋኒስታን፣ በባንግላዴሽ፣ በሰሜናዊ ሶርያ፣ በፍሊስጤም፣ በሊባኖስና በየመን ሀገራት ውስት ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን እንደሚከትብ ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።

ለእያንዳንዱ ሀገራት ዜጎችም እስከ 400 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ለማቅረብ እቅድ መያዙንም ገልጿል።

ለአብነትም ሂዩማን ራይትስዎች እንዳመላከተው፣ በፍሊስጤም የመጠለያ ጣቢዎች ከሚገኙት ዜጎች መካከል 18 በመቶ የሚሆኑት እና በሶርያ ደግሞ 17 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እስካሁን ድረስ ክትባቱን የወሰዱ መሆናቸውን አመላክቷል።

በመሆኑም በኳታር የሚገኘው ይህ መርጃ ድርጅት የጀመረው እንቅስቃሴ ክትባቱን ማግኘት ለማይችሉ የዓለም ሰዎች እንዲከተቡ በማድረጉ በኩል ትልቅ ተስፋ እንደተጣለበት ተገልጿል።

ገልፍ ኒዉስ

በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *