የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ስጋት የለም— የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

ከሰሞኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት ተሰልፈዉ ተመልክተናል፡፡

ብዙዎችም የነዳጅ እጥረት አለ የሚል ሃሳብ ሲሰነዝሩ ይሰማሉ፡፡

ይሁን እንጂ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ምንም አይነት የነዳጅ አቅርቦት ችግር የለም እያለ ነዉ፡፡

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጥራት፣ ንግድ አሰራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ዴኤታዉ አቶ እሸቴ አስፋው እንደገለጹት ቀድሞ ይገባ ከነበረው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የነዳጅ ምርት በአሁኑ ሰዓት 3 ሚሊየን ሊትር በቀን ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ይገኛል።

በተጨማሪም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዲፖዎች በቂ ክምችት ያላቸው በመሆኑ በአቅርቦት ላይ ምንም ስጋት እንደሌለ ገልጸዋል።

በመዲናዋ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩት ሰልፎች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ እሸቴ ይህ የተፈጠረው አፋር አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ላይ ችግሩ በመቀረፉ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች በብዛት ወደ ሀገር እየገቡ ናቸው ብለዋል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ የነዳጅ ሚዲያዎችና ተጠቃሚዎች እጥረት እንዲፈጠር የሚያደረግ ተግባር እያከናወኑ መሆኑን ሚኒስትሩ ባደረገው ቁጥጥር በማረጋገጡ ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪም ይሁን የአቅርቦት ችግር ባለመኖሩ ሁሉም ተረጋግቶ ስራውን እንዲቀጥል ነዉ ጥሪያቸዉን ያቀረቡት፡፡

ሃላፊዉ ይህን ይበሉ እንጂ በዛሬዉ እለትም በርከት ያሉ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ኢትዮ ኤፍ ኤም ታዝቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.