ለሰባት ቀናት የሚዘልቅ ሀገር አቀፍ የጸሎትና የምሕላ መርሃ ግብር ሊካሄድ ነዉ፡፡

የጸሎትና ምህላ መርሀ-ግብሩ የተዘጋጀዉ በሃገሪቱ እየታዬ ያለዉን የፖለቲካ ዉጥረትና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መባባስን ተከትሎ ነዉ ተብሏል፡፡

ሀገር አቀፍ የጸሎትና የምሕላ መርሃ ግብሩም ከሚያዚያ 7/2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ ታዉቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንዳሉት፣ ለ7 ቀን የሚዘልቀው የጋራ የጸሎትና ምሕላ መርሃ ግብር የሚካሄደዉ አሁን እንደ ሀገር እምነትንና ብሔርን መሰረት በማድረግ እየገጠመ ያለውን ጥቃት ወደ ፈጣሪ ለማሳሰብም ጭምር ነዉ፡፡

በምሕላ ጸሎት መርሃ ግብሩ በሚኖረው የትምህርት መርሃ ግብር እንደ እስካሁኑ ቤተ እምነቶቹ በፈለጉት ሳይሆን ርዕሰ ጉዳይ ተመርጦ ለሁሉም በተመሳሳይ ይሰጣቸዋል ነዉ የተባለዉ።

በዚህም መሰረት ዓርብ ስለ ንስሃና መጸጸት፣ ቅዳሜ ሥለ ይቅርታና እርቅ፣ እሁድ ሥለ ርሕራሔና እዝነት፣ ሰኞ ሥለ ተስፋ፣ ማክሰኞ ሥለ እምነት፣ ረቡዕ ሥለ ፍቅር፣ ሐሙስ ሥለ ምስጋና ትምህርት እንዲሰጥ ይደረጋል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *