ሳን ሜትሮፖሊታን “መሪ” የተሰኝዉን ቦታ ጠቋሚ መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡

ሳን ሜትሮፖሊታን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የተባለለትን የናቪጌሽን መተግበሪያ በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል፡፡

የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሰይፈ ስላሴ አያሌዉ በሰጡት መግለጫ፣ “መሪ” የተሰኘዉ መተግበሪያ፤ በኢትዮጵያ ከተሞች ላይ ተግባራዊ እንደሚሆንና በየብስና በእግር የሚካሄድን እንቅስቃሴ ለመጠቆም የሚያስችል ነዉ ብለዋል፡፡

የናቪጌሽን ስርዓትን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ለማዳረስም፣ በተንቀሳቀሽ ስልኮች አማካኝነት የቦታ ጠቋሚ መተግበሪያዉን መጠቀም እንደሚቻል ስራ አስኪያጁ አስታዉቀዋል፡፡

የመሪ መተግበሪያ በኢትዮጵያ ከመሰራቱም በተጨማሪ ለአጠቃቀም ምቹ እና አዳዲስ ቦታዎችን ለማወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የፍጥነት ገደብን የሚቆጣጠርና በዚህም የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንደሚኖረዉም ታምኖበታል፡፡

ደንበኞች መተግበሪያዉን ከጎግል ፕሌይ ስቶር በማዉረድ መጠቀም እንደሚችሉና ለ15 ቀናት በነፃ ከተጠቀሙ በኋላም በወር 49 ብር በመክፈል የተለያዩ አካባቢዎችን ማወቅ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ከዚህ ባሻገርም የመሪ መተግበሪያ ያለ በይነ መረብ በአጭር የፅሁፍ መልእክት አማካኝት እንደሚሰራና በአማረኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ሰምተናል፡፡

ይህ የቦታ ጠቋሚ መተግበሪያ ሲዘረጋም በተለያዩ አካባቢዎች 1 መቶ ሺህ ኪሎሜትር በመጓዝ መረጃ እንደተሰበሰበም ታዉቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *