ጥናቱ በ10 አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ያመላክታል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ዓለም አቀፉ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም “አሊያንስ” በቀጣዩ ሃሙስ ዓለምአቀፍ የሀገራት የረሀብ ምጣኔ ደረጃን(Global Hunger Index) ለማዎቅ የሚያስችል ጥናት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በ2020 የድህነት መሰፈርቶችን መሰረት አድርጎ በሰራው ጥናት፣ በዓለም ከ107 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 92ኛ ስትሆን የረሀብ ደረጃዋ ደግሞ 26 ነጥብ 2 በመቶ ሲሆን ይህም በመመዘኛው መሰረት የከፋ ረሀብ ሊባል የሚችል እንደሆነ አስታውቋል።
እኤአ በ 2000 ኢትዮጵያ የረሀብ ደረጃዋ በመቶኛ 51 የነበር ሲሆን አሁን ላይ መሻሻሎች እንዳሉ አመልክቷል፡፡
ይሄው ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈረንጆች 2030 ድረስ ለረሀብ የሚያጋልጡ ነገሮችን በመለየትና በማጥናት በአለምአቀፍ የረሀብ መመዘኛዎች መሰረት በኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማደረግ ጥናቱን እንደሚጀምር ነው የገለፀው።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የድርጅቱ ቅርጫፍ አስተባባሪ ወ/ሮ ሳራ ወርቁ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ በ10 አመታት ውስጥ ረሀብን ዜሮ ለማድረግ የክትትል ስራዎችን እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለረሀብ አደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን በአለምአቀፍ መመዘኛዎች በመታገዝ የጥናት ውጤቶችን ከነመፍትሄዎቻቸውና አማራጮች ጋር ለማቅረብ እንሰራለን ብለዋል።
ይህም የኢትዮጵያ መንግስት ረሀብን ለማጥፋት በሚያደርገው ሂደት ውስጥ የማሻሻያ ፖሊሲዎችን፣ እቅጣጫዎችንና መፍትሔዎችን ለመጠቆም ይረዳል ብለዋል።
በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም











