በጀርመን ግሩፕ ኤስ በመባል የሚታወቀው የሽብር ቡድን የፍርድ ሂደት መጀመሩ ተነግሯል፡፡
ትናንት በጀርመን ስቱትጋርት ከተማ ቀኝ ዘመም አክራሪ የሽብር ቡድን ነው የተባለው ግሩፕ ኤስ የፍድ ሂደት መጀመሩን የገለጸዉ ቢቢሲ ነዉ፡፡
ከ 32 እስከ 61 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት እነዚህ 11 ተጠርጣሪዎች፣ በስደተኞች፣በእስልምና እምነት ተከታዮች እና በፖለቲከኞች ላይ ጥቃት በማድረስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመቀስቀስ እንደሞከሩ ተገልጿል፡፡
ቡድኑ 27 ፈቃድ የሌላቸው ጦር መሳርያዎች የተገኘባቸው ሲሆን፣ ሌሎች ጦር መሳርያዎችን ከ 2 ሺህ ጥይቶች ጋር በእጃቸው ለማስገባት በዕቅድ ላይ ነበሩ ነዉ የተባለዉ፡፡
ለቡድኑ የቁሳቁስ ድጋፎች ሲያደርግ ነበር የተባለ የቀድሞ የፖሊስ መኮንንም ክስ ተመስርቶበታል፡፡
በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም











