በጅቡቲ ጀልባ ተገልብጦ የ34 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ ስደተኞች ተቋም (IOM) ከሆነ ስደተኞችን የጫነ ጀልባ በጅቡቲ ተገልብጦ ቢያንስ 34 ሰዎች ሞተዋል፡፡

ጀልባዋ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ስትመራ የነበረ ሲሆን፣ በየመን የነበረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ጅቡቲ እየተመለሱ ያሉ 60 ስደተኞችን ጭና ነበር፡፡

ጀልባዋ የተገለበጠችበት ምክንያት እስካሁን አልታወቀም፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ ስደተኞች ተቋም (IOM) በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት አፍሪካውያን ስደተኞች ስራ ፍለጋ ወደ ገልፍ ሀገራት የሚያደርጉት አደገኛ ጉዞ በጣም እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ሀገራት ድንበራቸውን በመዝጋታቸው ብዙ ስደተኞች ከተሰደዱበት ለመመለስ እየተገደዱ ነው፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በየመን በአደገኛ ሁኔታ ወጥመድ ውስጥ ከመሆናቸውም በላይ፣ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ለህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ተጨማሪ ክፍያ ለመክፈልም እየተገደዱ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ወር ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ጅቡቲ ወደብ ላይ 80 ስደተኞችን ከጀልባው ገፍትረው በሚያወርዱበት ወቅት፣ቢያንስ 20 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ አስራት
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.