ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምርምራ በማድረግ ከአፍሪካ ምን ያህል ደረጃ አላት?

ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች የምዕራባዊያን ሀገራት በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎችን ባትመረምርም ከአፍሪካ ግን የተሻለ ምርመራ እያደረጉ ከሚገኙ ሃገራት ዉስጥ ናት ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ምርምራ በማድረግ ከ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ቀጥላ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የኮቪድ19 ጥናት እና ምርምር ግብረ ሃይል አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር አበባው ገበየሁ ተናግረዋል፡፡

እርሳቸው እንዳሉት በመመርመር አቅም ይህን ደረጃ ብትይዝም፣ በሃገሪቱ አሁን ያለው የኮቪድ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዉ ሰዎች የሚያደርጉት ጥንቃቄ ደግሞ ቀንሶ መታየቱን አንስተዋል፡፡

ዶ/ር አበባው እንዳሉት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን፣ ለስድስት ወር ያህል የዳሰሳ ጥናት አደርጎ ነበር ብለዋል፡፡

በተጠናውም ጥናት በአዲስ አበባ 15 አካባቢዎች ላይ በተደረገ ዳሰሳ ማስክ ማድረግ 40 በመቶ ፣ ርቀትን መጠበቅ 20 በመቶ እንዲሁም እጅን መታጠብ 10 በመቶ ብቻ ተተግብሮ ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ይህም ቢሆን በአዲስ አበባ የተሻለ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አበባዉ በክልሎች ማለትም በአሶሳ ፣ አዳማ ፣ ጅማ በሁለተኛው እንደሚቀመጡ አንስተዋል፡፡

ሰመራ ፣ ባህር ዳር ፣ መቀሌ ፣ ጎንደር ፣ወላይታ ሶዶ፣ ጅግጅጋ ደግሞ ዝቅተኛ እና የመጨረሻው ረድፍ ላይ ተቀምጠዋል ብለዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.