ሱዳን ከዚህ በኋላ በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ የተሳሳተ አጀንዳ እንደማይኖራት ኢትዮጵያ አስታወቀች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ፣ካርቱም በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቂ ማስረጃ ስላገኘች ከዚህ በኋላ የተሳሳተ አጀንዳ ልትፈጥር አትችልም ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት እንዳዳሉት ፣በግድቡ ደህንነት እና የውሃ ሙሌት በተመለከተ በቂ መረጃዎች ተሰጥቷታል ነው ያሉት።

በመሆኑም ሱዳን የምትፈልገውን መረጃ በማግኘቷ ከዚህ በኋላ የተሳሳተ አጀንዳ ትከተላለች የሚል እምነት የለንም ብለዋል።

የግድቡ መገንባት ለሱዳን ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለዉ ጠንቅቃ ብታውቅም፣ በሌሎች ጫና ምክንያት የተሳሳተ አጀንዳ ስትፈጥር እንደነበርም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የግድቡን ሙሉ መረጃዎች፣ የግድቡን ደህንነት እና የውሃ ሙሌት በተመለከተም ለሱዳን መረጃ እንደሰጠች አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

የህዳሴው ግድብ መገንባት ብቻም ሳይሆን የተከዜ ግድብም ሱዳንን ከጎርፍ እንደታደጋት ጠንቅቀው እያወቁ በሌሎች ግፊት ድርድሩን እንዲስተጓጎል ማድረጓ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከድንበር ውዝግብ ጋር በተያያዘም ጦርነት ለሁለቱም አገራት ስለማይጠቅም በድርድር ይፈታል የሚል አቋሟን እንደቀጠለች ቃል-አቀባዩ አንስቸዋል።

በአባቱ መረቀ
ሚያዝያ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *