ሶማሊያ በውስጥ ጎዳዬ ማንም ጣልቃ እንዲገባ አልፈቅድም ብላለች፡፡

የሶማሊያ መንግሥት የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ማራዘሚያ ውሳኔ እንደጸና በመግለጽ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ሂደቶች ለማደናቀፍ እየፈለገ ነው ሲል በብርቱ ተችቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው፣ ከአንዳንድ ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው በሰጡት መግለጫ መደናገጣቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህንን የእኛን ውሳኔ እኚህ ሀያላን ሀገራት “በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል” ብሏል፡፡

የብሔራዊ ተቋማትን የፖለቲካ ነፃነት እና ሉዓላዊ መብቶች የሚሸረሽሩ በማስፈራራት የተሞሉ የብጥብጥ መግለጫዎች፣ በሶማሊያ ውስጥ አሸባሪ ድርጅቶችን እና ፀረ-ሰላም አካላትን ለማበረታታት ብቻ ያገለግላሉ እንደሁን እንጂ ይህ ለእኛ አንዳችም ጥቅም የለውም ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

ይህንን የፓርላማ ውሳኔ ዓለም አቀፍ አጋሮቻችን መደገፍ አለመቻላቸውም ብሏል፡፡

የሶማሊያ የታችኛው ምክር ቤት ሰኞ እለት የፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የስልጣን ዘመን እና የፌደራል ፓርላማውን ለሁለት ዓመታት ያህል ማራዘሙ ይታወሳል እንደ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ ፡፡

ይህንን ውሳኔ በሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎች እና በጅቡቲ እና በፑንትላንድ ክልላዊ መንግስታት እንዲሁም የሀገሪቱ ሴኔት ተችቷል ፡፡

የሶማሊያ ለጋሾች አሜሪካን እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ውሳኔውን ከፋፋይ እና የሀገሪቱን መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላል ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

በውጤቱም ሁለቱም ከአገሪቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደገና እንደሚያጤኑ ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.