ድጋፉ ግን “በወታደራዊ ኃይል” አይደለም ብለዋል ባይደን፡፡
የአሜሪካው የአየር ድብደባ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 2001 እንደተጀመረ ከተነገረበት ከነጩ ቤተ-መንግስት ክፍል ውስጥ ሆነው ባስተላለፉት መልዕክት፣ “የአሜሪካን ረጅሙን ጦርነት ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው” ብለዋል፡፡
ይህ የባይደን ውሳኔ ከ2001 የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት 20ኛ ዓመት ጋር መገጣጠሙን ባለስልጣኖች አስታውቀዋል፡፡
ቢያንስ 2 ሺህ 500 የአሜሪካ ወታደሮች የ9ሺህ 600 ጠንካራ የኔቶ አፍጋን ተልዕኮ አካል መሆናቸዉ ይነገራል፡፡
በአፍጋኒስታን መሬት ላይ ያሉት የአሜሪካ ወታደሮች ቁጥር ይለዋወጣል ፣ እናም የአሜሪካ ሚዲያዎች የአሁኑ አጠቃላይ ድምር ወደ 3 ሺህ 500 ይጠጋል ሲሉ ዘግበዋል፡፡
የአሜሪካ እና የኔቶ ባለሥልጣናት ታሊባን ፣ በአፍጋኒስታን ጥቃቶችን ለመቀነስ የገባውን ቃል እስከ አሁን አላሟላም ብለዋል፡፡
የካቡል ባለስልጣናት በበኩላቸው የአፍጋኒስታንን ሰላም ለማረጋገጥ የሰላም ውይይቶችን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
ቢቢሲ
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 07 ቀን 2013 ዓ.ም











