የሩሲያዉ መልእክተኛ በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ‘ረሃብ የለም’ ብለዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ማዕቀቦች የተደራረቡባት ሰሜን ኮሪያ አሁን ደግሞ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ድንበሮችን በመዝጋቷ የውጭ ንግድ እንቅስቃሴ ቆሟል፡፡

ይህንንም ተክትሎ በፒዮንግያንግ ሕይወት አስቸጋሪ እንደሆነ በሰሜን ኮሪያ የሩሲያ አምባሳደር ተናግረዋል።

ያም ሆኖ ግን በሰሜን ኮሪያ ረሃብ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሩሲያው TASS የዜና ወኪል የታተመው የአሌክሳንደር ማትጎራ አስተያየት የተሰማው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው “ከመቼውም ጊዜ የከፋ ሁኔታ” እንደገጠማት ከተናገሩ በኋላ በሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ኪም የገዢው ፓርቲ ባለሥልጣናትን በ1990ዎቹ ተከስቶ ከነበረው ረሃብ እና አደጋ ጋር የአሁኑን የኢኮኖሚ ቀውስ በማገናኘት፣ ከፍተኛ ሥራ እና መስዋእትነት እንዲከፍሉ አሳስበዋል፡፡

በሀገሪቱ ካሉ ጥቂት የውጭ መልዕክተኞች መካከል የሩሲያ አምባሳደር በሰጡት አስተያየት አሁን ያለው ሁኔታ ከዚያ ዘመን ጋር ሊወዳደር የሚችል አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡

“እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ፣ ከአስጨናቂው መጋቢት ረጅም ርቀት ላይ ነው ያለነው ፣ እናም በጭራሽ ወደዚያ እንደማይመጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል ፡፡

በ1990ዎቹ መጨረሻ እዚህ የተከሰተውን በደንብ አስታውሳለሁ የሚሉት የሩሲያዉ መልዕክተኛ እናም ማወዳደር እችላለሁ፣ከዚያ ጊዜ ጋር የሚወዳደር አይደለም ብለዋል፡፡

አክለውም “በጣም አስፈላጊው ነገር ዛሬ በአገሪቱ ውስጥ ረሃብ አለመኖሩ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በሯ ለበርካታ ሀገራት ዝግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማዕቀብ የደቀቀዉን ኢኮኖሚዋ ላይ የኮሮና ቫይረስ ተዳምሮ ከፍተኛ ረሃብን ሊያስከትል ይችላል የሚሉ መረጃዎች እንዳሉም ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *