የሸገር ድጋፍ ሰጪ ትራንስፖርት የኪራይ ውሉ ለተጨማሪ ሁለት ወራት ተራዘመ፡፡


የኪራይ ብር መጠኑም መሻሻሉ ተነግሯል፡፡
የሸገር ድጋፍ ሰጪ ትራንስፖርት ጥቅምት ዘጠኝ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ውል ገብቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

ዉሉ በሰአቱ ሲፈጸም ለስድስት ወራት እንዲዘልቅ ታስቦ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ካለው የትራንስፖርት ችግር አኳያ ኪራዩን ጨምሮ ማራዘም ማስፈለጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ሃላፊ የሆኑት ኢንጅነር ስጦታው አካል ገልፀዋል።

በተያያዘም አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ፣ ለአንድ ድጋፍ ሰጪ አውቶብስ ሁሉንም ሂደት ታሳቢ አድርጎ አራት መቶ ሰባት ብር ማሻሻያ ተደርጓልም ብለዋል።

በኪራዩ ላይ ማሻሻያ ቢደረግም ህብረተሰቡ ላይ ቀድሞ ከሚከፍለዉ ዉጭ ጭማሪ አለመደረጉን አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚስተዋለዉን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል 500 የሚጠጉ አዉቶቡሶችን በኪራይ ወደ ትራንስፖርት አገልግሎት ማስገባቱ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ በኪራይ የገቡት ከ 5 መቶ የሚጠጉ ቢሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች በስራ ላይ ያሉት ግን 350 የሚጠጉት ብቻ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.