አሁንም ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ይኑር ብለን ባገኘነው ጊዜ ሁሉ እየተናገርን ነው አሉ የኦፌኮው ተቀዳሚ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፡፡

ፖርቲው ከ2013 ቱ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ራሱን ካገለለ በኃላ ስለሚያደርገው እንቅስቃሴና ቀናትን ስላስቆጠረው የምረጡን ክርክር አስተያየት እንዳለው ኢትዮ ኤፍ ኤም ጠይቋል፡፡

ፕሮፌሰር መረራ “ አሁንም መደራጀታችንን ፤መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎችን መግፋታችንን እና አሁንም ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይኑር ብለን ባጋጠመን ጊዜ ሁሉ እየተናገርን ነው” ብለዋል፡፡

‹‹ለዚህ ሀገር ትልቁ እና ዋናው መፍትሔ ብሔራዊ መግባባት ነው በሚለው አቋማችን አንደፀናን ነው ፡፡

እኛ አሁንም ሰላማዊ ትግሉን አጥብቀን ይዘናል ›› ያሉት ተቀዳሚ ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ፡፡

መንግስት ቢዋጥለትም ባይወጥለትም ቁጭ ብሎ መነጋገርን መድፈር ይኖርበታል ሲሉ ያክላሉ በሰከነ አእምሮ ቁጭ ብሎ ምንድነው መሰረታዊ ችግሮቻችን ደግሞስ እንዴት እንፍታ የሚለውን መነጋገር በጣም ወሳኝ ነው ይላሉ፡፡

የምረጡኝ ክርክሮችን ተመልክተዋል ወይ ? ምን ተንጸባረቀ ? ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ ፕሮፌሰር መረራ ‹‹እውነት ለመነጋገር እውነተኛ አቋም ያላቸውና ያንንም ጥሩ አድረገው የሚያነሱ አሉ ፤የዚያኑ ያህልም ደግሞ ቲያትር መሳይ ነገር የሚያሳዩ አሉ፡፡ እየኮመኮምኩ ነው›› ብለውናል፡፡

እናንተ በዚህ ክርክር ላይ ብትኖሩ ምን ይፈጠር ነበር? ላልናቸውም ‹‹ከመጀመሪያው ልዩነት እንደሚፈጠር ስለታወቀ መስሎኝ የጅምላ እስር የተደረገው›› ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.