የሰሜን ሸዋ አስተዳደር ችግሩ ከአቅም በላይ ሆኖብኛል የፌደራል መንግስቱን ድጋፍ እንፈልጋለን ብሏል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ እና አካባቢዋ የተፈጠረው የታጣቂዎች ጥቃት በድጋሚ አገርሽቶ በርካቶች ህይወታቸው እንዳጡ እየተነገረ ነው፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻዲቅ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣ ዛሬ 3ኛ ቀኑን የያዘው የታጣቂዎች ጥቃት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል ብለዋል፡፡

የተረፉትም ህይወታቸውን ለማዳን ከተማውን ለቀው እየወጡ መሆኑን አረጋግጠውልናል፡፡

መንግስት አስቸኳይ እርምጃ ወስዶ ሀይል ካልመደበ ችግሩ ከዚህም በላይ ይከፋል ያሉት አስተዳዳሪው ከአቅም በላይ ሆኖብናል ሲሉም አክለዋል፡፡

ታጣቂዎቹ የተደራጁ መሆናቸዉን ገልጸዉ፣ የአጣዬና አካባቢዋ ነዋሪዎችም መንግስት በቂ ሀይል ያሰማራልን ስንል ያቀረብነውን ጥያቄ ሊሰማን አልቻለም ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እንዳሉት ሰዎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነዉ፤ቤቶች ወድመዋል፤ ታጣቂዎች በተደራጀ መልኩ በመኪና እንደሚመጡ ሰምተናል ሲሉም ነግረውናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *