የግብፅና የጂቡቲ ፕሬዚዳንቶች በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ እና የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ትናንት በስልክ ተወያይተዋል፡፡

የቀጠናው ጸጥታና መረጋጋት በምንም መልኩ እንዳይነካ ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሁለቱ አገራት መሪዎች መስማማታቸውን ከግብፅ ይፋ የሆነው ሚና የዜና አገልግሎት ዘግቧል ሲል አናዶሉ አስነብቧል፡፡

በውይይቱ ወቅት አል ሲሲ በግድቡ መሙላት እና ሥራ ላይ አስገዳጅ እና ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ለዘጠኝ ዓመታት ግብፅ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በግድቡ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ቢቆዩም ዉይይቶች ጠብ ያለ መፍትሔ አላስገኙም፡፡

አዲስ አበባ ግድቡ ከካይሮ እና ከካርቱም ጋር ባያግባባትም ግድቡን እንደምትሞላ አጥብቃ ትናገራለች፡፡

ግብፅ እና ሱዳን በተለይም በአባይ ውሃ ዓመታዊ ድርሻቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያሳርፍ በመጀመሪያ የሶስትዮሽ ስምምነት ላይ መደረስ አለበት ይላሉ ፡፡

አባይ የማያልፍባት ጅቡቲ የተወሰኑትን የውሃ ፍላጎቶቿን ከኢትዮጵያ የምታሟላ ሲሆን ጅቡቲም በአባይ ላይ የሚደረገውን የግድብ ግንባታ እንደምትደግፍ ታውቋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *