ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና ታምራት የማነ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተገለጸ፡፡

የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሯል፡፡

ልዩ ዘመቻዎች ሃይል 2ኛ ኮማንዶ ብርጌድ 3ኛ ኮማንዶ ሻለቃ በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ዘመቻ አመርቂ ግዳጅ መፈፀማቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የ3ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ሻለቃ ደረጄ ዴቢሳ እንደገለፁት ፣ በትግራይ በተደረገው ህግን በማስከበር ዘመቻ ጠላት የሚመካባቸውን ምሽጎች በሶሮቃ ፣ በዳንሻ ፣ በባካር ፤ በመሶበር ፤ በጨርጨርና በአይደፈር ተራሮች ላይ የተገነቡ ምሽጎችን በመስበር የጠላትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል፡፡

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር መዋቅር ውስጥ በመሆን ከፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር እየሰሩ የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ኢዲቶሪያል ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በመቀሌ ከተማ በግለሰብ ቤት ስቱዲዮ ተከራይተው የውሸት ፕሮፓጋንዳ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፉ እያሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

በግለሰቦቹ ቤት በተደረገው ፍተሻም ለህወሃት ታጣቂ ቡድን ወደ በረሃ ለመላክ የተዘጋጁ በርካታ መድሀኒቶች ፤ አልባሳትና የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ የኤሌክትሮኒክ እቃዎችና በርካታ ዶክመንቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አዛዡ ተናግረዋል።

መረጃው የመከላከያ ሚኒስቴር ነው

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *