በኒጀር በደረሰ ጥቃት የ19 ሰዎች ህይዎት አለፈ፡፡

በምዕራባዊ ኒጀር ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የ19 ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸዉ ታዉቋል፡፡

ጋይጉሩ በተሰኘችዉ የአገሪቱ መንደር ተሸርካሪ ላይ ሆኖ አንድ ታጣቂ በከፈተዉ ተኩስ ዜጎቹ መገደላቸዉንም ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ኢብራሂም ካቴላ ሲናገሩ ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከጎረቤት አገር ማሊ የመጡ ናቸዉ ብለዋል፡፡

እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለም ነዉ ዘገባዉ ያስታወቀዉ፡፡

በኒጀር ባለፈዉ ወር በተመሳሳይ 13 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸዉ የሚታወስ ሲሆን በዚህ አመት ብቻ ደግሞ ከ3 መቶ በላይ ዜጎች ህይዎታቸዉን አጥተዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

የአገሪቱ መንግስትም የታጠቁ ሃይሎች የንፁሃንን ህይዎት እየቀጠፉ ቀጠናዉን ወደ ትርምስ አስገብተዉታል ማለቱን ዘገባዉ አስፍሯል፡፡

ኒጀርን ጨምሮ በሌሎች የሳህል ቀጠና አገራት በታጣቂዎችና በሽብር ቡድኖች አማካኝነት በየቀኑ በርካታ ንፁኃን ዜጎች ህይወታቸዉን እያጡ መሆኑን ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.