በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር ቪልማ ቶማስ ደሴቲቱ በአሜሪካ ኢኮኖሚያዊ፣ ንግድ እና ፋይናንስ እገዳ ምክንያት በምታደርገው ትግል የዚህች ሀገር ታሪካዊ ድጋፍ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል፡፡
የኩባ አምባሳደር ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ ከ 60 ዓመታት በላይ የዘለቀውን ይህንን እቀባ በተመለከተ የምታሰማው ተቃውሞ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እና በአፍሪቃ ህብረት እንዲሁም በሌሎች የብዙ ሁለገብ መድረኮች ላይ መታየቱን አስረድተዋል ፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዲፕሎማቱን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ዋና ጽህፈት ቤት ተቀብለው በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙሪያ የተነጋገሩ ሲሆን በስትራቴጂክ ዘርፎች ትብብርን የማስፋፋቱ አስፈላጊነትንም ጠቁመዋል ሲል ያስነበበው Prensa Latina ነው ፡፡
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም











