የሞሮኮ ባህር ሃይል በሜድትራኒያን ባህር ወደ ስፔን ሲያቀኑ የነበሩ 165 ስደተኞችን ማዳን መቻሉን አስታወቀ፡፡

የሞሮኮ ባህር ሃይል ጠባቂዎች ካተረፏቸው ስደተኞች መካከል ከሰሃራ በታች 103 ሰዎችን ፣ 34 የሚደርሱ ሞሮኮያውን ፣ እንዲሁም 27 የባንግላዲሽ ዜጎችን ማትረፍ መቻላቸውን MAP የተሰኘውን የሞሮኮ የዜና ምንጭን በመጥቅስ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ሜዲትራንያን ወደ አትላንቲክ የሚጓዙ ስደተኞች በርካታ ጊዜ የተሳፈሩባቸው ጀልባዎች ችግሮች እንደሚያጋጥማቸው ዘገባው አክሏል፡፡

እነዚህ ስደተኞችም በከፍተኛ ሁኔታ ከሚደርስባቸው ጉዳት መትረፍ መቻላቸውን ነው ያስታወቀው ዘገባው፡፡

አብዛኛዎቹ ስደተኞች ሞሮኮን ወደ አውሮፓ ለመድረስ ለሚፈልጉ የአፍሪካ እና የእስያ ስደተኞች መተላለፊያ አገር አድርገው ይጠቀሟታል፡፡

ምክንያቱም ከሞሮኮ ሜዲትራንያን የባህር ዳርቻዎች እስከ ስፔን ያለው አጭሩ ርቀት በጊብራልታር ወንዝ በኩል 14 ኪ.ሜ ብቻ ነው ፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

ሚያዚያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *