የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በሀገሪቱ ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫን ለማድርግ በሚያስችለው የውይይት ሂደት ላይ የአፍሪካ ህብረት እንዲመራ ጥሪ አቅረበዋ ሲል ቢቢሰ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የወደፊቱ የአገሪቷ ዴሞክራሲ በሚወስነው በዚህ ውይይት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ፡፡
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሆኑትን የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ተሺክዲን ጋር ተገናኝቷል ላይ ናቸው፡፡
ፕሬዝደንት ፋርማጆ ባለፈው ሳምንት ፓርላማው የወሰነውን የስልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት የማራዘም ውሳኔ አፅድቀዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ማራዘሚያውን አውግዟል፡፡
በክልሎች እና በፌዴራል መንግስታት መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ በሶማሊያ ምርጫው እንዲዘገይ ተደርጓል፡፡
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም











