የቻዱ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ በጥይት ተመተዉ መሞታቸዉ ተነገረ፡፡

በቅርቡ በአገሪቱ የተደረገዉን ምርጫ ድጋሜ ያሸነፉት የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ፣ ከአማፅያን ሃይሎች ጋር በነበረ የተኩስ ልዉዉጥ ቆስለዉ መሞታቸዉን የአገሪቱ መንግስት አስታዉቋል፡፡

የ68 አመቱ ፕሬዝዳንት ዴቢ ለአገራቸዉ ሉአላዊነት ሲሉ ከአማፅያን ጋር በጦር ግንባር ሲፋለሙ ህይወታቸዉ ማለፉንም የአገሪቱ መከላከያ ቃል አቀባይ ጀነራል አዚም በርማዶዋ አጉና ተናግረዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱን ህልፈተ ህይወት ተከትሎም ልጃቸዉ ጀነራል ማሃማት ካካ ጊዚያዊ የቻድ መሪ እንዲሆኑ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ዴቢ በ1990 ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን በቅርቡም ለስድስተኛ ጊዜ ተወዳድረዉ ምርጫዉን ማሸነፋቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በቻድ አማፅያኑ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሱ እንደሚገኙ የዘገበዉ አልጄዚራ፤ ባለፈዉ ቅዳሜም ከመንግስት ወታደሮች ጋር በነበረዉ የተኩስ ልዉዉት ከ 3 መቶ በላይ አማፂ ሃይሎች ሲገደሉ ከመንግስት በኩል ደግሞ 5 ወታደሮች መሞታቸዉ ተነግሯል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሚያዝያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *