በሊቢያ የነዳጅ ዘይት ወደቦች ላይ ጉዳት እያጋጠመ መሆኑ ተነገረ።

የሊቢያ ብሔራዊ የነዳጅ ዘይት ኮርፖሬሽን እንዳለው በዋና ዋና የነዳጅ ወደቦች ላይ የሃይል መቆራረጥ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እየተከሰተ ነው ብሏል።

በመንግስት የሚተዳደረው የሊቢያ የነዳጅ ዘይት ኮርፖሬሽን (NOC) እንዳስታወቀው፣ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የነዳጅ ወደቦች አንዷ በሆነችው በሃሪጋ ወደብ ላይ የኃይል አቅርቦት ጉዳት መከሰቱን አስታውቋል፡፡

የሊቢያ ማዕከላዊ ባንክም የነዳጅ ዘይቱ በሚገኙባቸው ወደቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለማካካስ ምንም አይነት ተጨማሪ በጀት ለመመደብ ፈቃደኛ ያለመሆኑን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ባለፈው ዓመት በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈው የሊቢያ መንግስት 230 ሚሊዮን ዶላር ለ NOC ለመመደብ መወሰኑን የዥንዋ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ወደ ተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚላከው የነዳጅ ዘይት በሃሪጋ ወደብ በደረሰበት የኤሌክትሪክ ጉዳት በየቀኑ ከ 118 ሚሊዮን ዲናር በላይ ወይንም (26 ሚሊዮን ዶላር) ገቢ ሊያሳጣ እንደሚችል NOC በመግለጫው አስታውቋል፡፡

የበጀት እጥረት በሃገሪቱ በሚገኙ የNOC ኩባንያዎች ዕዳ ማስከተሉም የተነገረ ሲሆን፣ በዚህም ወደ 280 ሺህ በርሜል ገደማ በየቀኑ የሚመረተው የዘይት ምርት ሊቀንስ መቻሉ ተነግሯል ፡፡

ድርጅቱ ለሃገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት በፃፈው መግለጫ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የ NOC ሥራዎችን የሚያደናቅፉት አካላት ሁሉ በሕግ እንዲጠየቁና የአገሪቱን አቅም አደጋ ላይ ለመጣል እንዲሁም የሊቢያ ብቸኛ የገቢ ምንጭ የሆነውን የነዳጅ ዘይት ምንጭ ለመጉዳት በሚሞክሩ ላይ አስፈላጊ የሕግ እርምጃዎችን እንዲወስድ ሲል ጠይቋል፡፡

ዥንዋ

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሚያዚያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.