በትላንትናው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ፡፡

በትላንትናው እለት ኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የ 12 የመኖርያ ቤቶች ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን በአደጋውም አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አቶ ጉልላት እንዳሉት በከተማዋ በትላንትናው እለት አንድ የእሳት አደጋ መድረሱን አስታውቀው፤ አደጋው 300 ካሬ የሸፈነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በደረሰው አደጋ 1 ሚሊዮን ብር ሲወድም 13 ሚሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በ 2 ሰዎች ላይም አንድ ቀላልና አንድ ከባድ የመቁሰል አደጋ አጋጠሟቸዋልም ብለዋል፡፡

አደጋውን ለመቆጣጠር 27 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፣ 4 ከባድ መኪናዎች እና 1 አምቡላንስ አብረው እንደተሰማሩ እና ለእሳቱ ማጥፊያ 21 ሺህ ሌትር ውሃ ጥቅም ላይ መዋሉንም ገልጸዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እስካሁን አለመታወቁን አቶ ጉልላት ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *