የውጭ ዜና

ዴሪክ ቾቪን በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ፡፡

ዴሪክ ቾቢን ባለፈው ዓመት በሚኒሶታ ጎዳና ላይ አፍሪካ አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን ትከሻው ላይ በመጫን ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን ተከትሎ በዓለም ላይ በጥቁሮች ላይ የሚታየውን ዘረኝነት የሚያወግዝ ታላቅ የእንቅስቃሴ ተቃውሞ ተካሂዷል፡፡

ለዚህ ንቅናቄ ዘመቻ ምክንያት የሆነው የጆርጅ ፍሎይድ ሞት ተጠያቂው ዴሪክ ቾቢን የተሰኘው የሚኒያ ፓሊስ ለህግ እንዲቀርብ በርካቶች ጩኃታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡

ለዘህ ፍርድ የተሰኘመው ዳኛም ዴሪክ ቾቪን ግድኛውን ስለመፈፀሙ አረጋግጧል፡፡

የ 45 ዓመቱ ዴሪክ ቾቪን በሶስት ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱ የተነገረ ሲሆን በሶስቱም ክሶች በግድያ ወንጀሉ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆኖ መገኘቱ ነው የተነገረው፡፡

ገዳዩ እስኪፈረድበት ድረስም በእስር ላይ እንደሚቆይ እና ለአስርት ዓመታት ያክል የእስር ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተነግሯል፡፡

የፍርድ ሂደቱን ተከትሎ በርካቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡

የፍሎይድ ቤተሰቦች በበኩላቸው ይህ ለአሜሪካ በርግጥም ትልቅ የታሪክ ለውጥ ምልክት ነው ብለውታል፡፡

ፕሬዝዳንት ጆ ቫይደን እና ምክትላቻ ካማላ ሀሪስ በበኩላቸው ከፍርድ ውሳኔው በኋላ የፍሎይድ ቤተሰብን ጠርተው ማናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡

ፕረዝደንት ጆ ቫይደንም ቢያንስ አሁን ጥቂት የሚባል ፍትህ አለ ሲሉ ተደምጠዋል ፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ይህ እውነተኛ የፍትህ ስርዓት ዘረኝነትን ለመቋቋም የመጀመሪያ እንቅስቃሴያችን ይሆናል ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ በአሜሪካ ውስጥ የፖሊስ የስራ ሁኔታን ለማሻሻል የተቋቋመውን ረቂቅ ሕግ እንዲያፀድቁ አሳስበዋል ፡፡
እንዲሁም ጉዳዩን ተከታትለው ትክክለኛ ውሳኔን ለወሰኑ ዳኞችን አመስግነዋል ፡፡

ቢቢሲ

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሚያዚያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *