አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች የተሰጣቸውን የአየር ሰዓት በትክክል መጠቀም አልቻሉም ተባለ።

ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8ን ጨምሮ በሃገሪቱ በሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ለ 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ተፎካካሪ የሆኑ የፓለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ቅስቀሳ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ድልድል መሰረት በየመገናኛ ብዙሃኑ የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ።

ይሁንና ኢትዩ ኤፍ ኤምን ጨምሮ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎቹ፣ ቅስቀሳቸውን በሚያካሂዱባቸው መገናኛ ብዙሃኖች ላይ፣ የተሰጣቸውን የአየር ሰዓት በተገቢው እየተጠቀሙበት እንዳልሆነ መገናኛ ብዙሃኑ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ፣ ፓርቲዎቹ ሲያካሂዱበት የቆየውን የአየር ላይ ቆይታ ምን መልክ እንደነበረው አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በበኩሉ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ፣ ፓርቲዎቹ እስካሁን በአጠቃላይ ከተመደበላቸው የአየር ሰዓት መጠቀም የቻሉት በአማካኝ 53 በመቶ ያክሉን መሆኑን አስታውቋል።

ስለሆነም አንዳንድ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎቹ፣ በየመገናኛ ብዙሃን የተሰጣቸውን ነፃ የአየር ሰዓት በሚፈለገው ልክ እየተጠቀሙ አይደለም የሚል ቅሬታ ቀርቦባቸዋል።

ፓርቲዎቹ በበኩላቸው ከመገናኛ ብዙሃኑ ለቀረበባቸው ቅሬታ፣ የተለያዩ ምላሾችን የሰጡ ሲሆን፣ ከምንም በላይ ደግሞ የአቅም ማነስ ችግር ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነባቸው ተናግረዋል።

የተሰጠን የአየር ሰዓት ድልድል ጥሩ ቢሆንም፣ በተቃራኒው በባለስልጣኑ ተዘጋጅቶ የተሰጠን ፎርማት ምቹ ያለመሆኑ፣ በተለይም ቅስቀሳው በቅጂ መሆኑ፣ የመገናኛ ብዙሃኑ ተደራሽነት በተለይም በክልሎች እንዲሁም የቋንቋ ችግር እና በሌሎችም ቴክኒካል ችግሮች ምክንያት ከምንም በላይ ደግሞ የአቅም ውስንነት እንዳለብን እወቁልን ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በበኩሉ በፓርቲዎቹ የሚነሱ ቅሬታዎችን እየፈቱና የተነሱ ቅሬታዎች ላይ በማተኮር በቀጣይ እንደሚሰራ የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር ተናግረዋል።

በዛሬው እለት የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፣እንዲሁም ፌድሪክ አበርት ስቱፍትኢንግ፣ በ 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ሂደን ላይ ምክክር አካሂደዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ። ድረ ገጻችንን

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሚያዝያ14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *