የመተከል ተፈናቃዮች የክረምት ወራት መቃረቡ ስጋት ላይ እንደጣላቸው ገለጹ::

ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ እና በጓንጓ ወረዳ ተጠልለው የሚገኙ ቁጥራቸው ከ77ሺ በላይ የሆኑ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የክረምት ወራት መቃረቡ ስጋ ላይ ጥሎናል ብለዋል፡፡

ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፑ የሚገኘው ወንዝ ዳር ከመሆኑ የተነሳ እንዲሁም መጪው የክረምት ወራት በመቃረቡ ስጋት ላይ እንደጣላቸው ለጣቢያችን ተናግዋል፡፡

መንግስት የአካባቢውን ሰላም አስጠብቄ በቅርቡ ወደ ቀዬያችሁ እመልሳችኋለሁ ያለ ቢሆንም በተግባር እየታየ ያለ ነገር የለም ሲሉ የጓንጓ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብርሀኑ መኮንን ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል::

ሀላፊው አክለውም ተፈናቃዮች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ስልጠና የተሰጣቸው ቢሆንም ከሥልጠናው በኋላ ቃል ራሳቸውን እና አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ በሚል ቃል የተገባላቸው መሳሪያ ግን ተፈጻሚ አልሆነም ብለዋል::

ጳጉሜ 2012 የጀመረው ቀውስ ቀስ በቀስ ዜጎችን ከቀዬያቸው ማፈናቀል ከጀመረ ከ7 ወራት በላይ አስቆጥሯል::

በመቅደላዊት ደረጀ
ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *