በአዲስ አበባ የመሬት አጠቃቀም ላይ በተደረገ ፍተሻ 13 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ያለአግባብ የተያዘ መሬት መለየቱን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
የመሬት ዘርፉን ከመልካም አስተዳደር ችግር ለማጥራት በተከናወነው ተግባርም 422 ሙያተኞች ከዘርፉ እንዲወጡ መደረጉ ተገልጿል።
በመሬት አሰጣጥ ፍተሻው 13 ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬት ያለአግባብ የተያዘ መሆኑን በማጣራት 10 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ ተደርጓል ተብሏል።
ምክትል ከንቲባዋ ጥያቄ ቀርቦባቸው ለረዥም ጊዜ ውሳኔ ያልተሰጣቸው 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የመሬት ይዞታዎች በአንድ ጊዜ ውሳኔ እንዲያገኙ መደረጉን ገልፀዋል።
ይህን መሰረት በማድረግ የመሬት ጥያቄ ለነበራቸው የሃይማኖት ተቋማት፣ በሆቴልና አገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ አዳዲስና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች፣ ለጤና ዘርፍ ተቋማት፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎችና መሰል ፕሮጀክቶች ግልጽ በሆነ አሰራር መሬት ተሰጥቷል ብለዋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም











