የአውሮፓ ህብረት ለደቡብ ሱዳን 51 ሚሊየን ዶላር መመደቡን አስታወቀ፡፡

ደቡብ ሱዳን ያለችበትን የርሀብ ወቅት እንድትቋቋም 51 ሚሊየን ዶላር መድቤያለው ሲል የአውሮፓ ህብረት ሲል አስታውቋል፡፡

ህብረቱ የመደበው ገንዘብ ለምግብ ፍጆታ፣ለሰው ሰራሽና ለተፈጥሮ አደጋዎች መቋቋሚያ እንደሚውል ተነግሯል፡፡

በደቡብ ሱዳን ያለው የሰዎች ሁኔታ እጅግ አስከፊ እንደሆነ የጠቆመዉ ዘገባዉ፣ጉዳዩ አሳሳቢና ትኩረት የሚሻው እንደመሆኑ በቂ የሆነ አለምአቀፋዊ ትኩረት አላገኘም ብሏል፡፡

እስካሁን ለደቡብ ሱዳን እጃቸውን የዘረጉት የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ 5 ለጋሾች ብቻ መሆናቸዉን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *