ይፋት የልማት ማህበር በአጣዬና አካባቢዋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ1ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።


ይፋት የልማት ማህበር ከአባላቱ ከኤፌሶን 2 “ጎፈንድ ሚ” እና ከአለን የበጎ አድራጎት ማህበር ያሰባሰበውን 1ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብና የንጽህና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

በመንዝ መሀል ሜዳና በርግቢ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ማድረሱንም የልማት ማህበሩ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደጀን መንገሻ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ማህበሩ ከዚህ በተጨማሪም የተጎዱ ዜጎችን ባለቡት ሆስፒታል ሄዶ መጎብኘቱ የተሰማ ሲሆን በጥቃቱ ሙሉ ለሙሉ የወደመችውን አጣዬ ከተማን ጎብኝቶም መረጃ እንዳሰባሰበም አቶ ደጀን ነግረውናል።

ይፋት ልማት ማህበር ከኤፍራታና ግድም የዞን አመራሮች ጋርም ውይይት አድርጓል ተብሏል።
በቀጣይ ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሆን መስራት ያለበትን ስራዎች መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል አስተባባሪው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
መቅደላዊት ደረጄ
ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *