አይነ ስውርነትን የሚያስከትለውን ትራኮማን ከሀገሯ በማስወገድ ጋምቢያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ሀገር መሆኗን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንዳመለከተዉ በዓለም ላይ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በዚህ ህመም ተጠቅተዋል፡፡
የጋምቢያ መንግስትና የእርዳታ ድርጅቶች በርካታ አመታት ቤት ለቤት በመዞር በተለይ በገጠራማ የሀገሪቱ ክፍል ህሙማንን የማከም ስራ መስራታቸውም በዘገባው ተካቷል፡፡
ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ በንክኪ እንደሚሰራጭ የሚነገረው ትራኮማ፣ በዓለም ጤና ድርጅት ከተለዩ ደሀ ሀገራትን ያጠቃሉ ከተባሉ 20 የጤና እክሎች ውስጥ የሚጠቀስ ነዉ፡፡
በዘመቻ መልክ ትራኮማ ላይ የተነሳችውና ድል ያደረገችው ጋምቢያም ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና ቀጥሎ ትራኮማን ማጥፋት የቻለች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም











