በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት ኤች አይ ቪ እያደረሰ ያለው ጉዳት ቸል መባሉ ተገለጸ።

ምርጫን ጨምሮ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ባሉ አሁናዊ ሁኔታዎች ኤች አይ ቪ ቫይረስ ትኩረት እንዲነፈግ ምክንያት ሆኗል ብሏል የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት።

ጽህፈት ቤቱ በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ባዘጋጀው የስልጠና መድረክ ላይ እንዳለው በአመት ከ12ሺ በላይ ዜጎችን እየነጠቀን ላለው ኤች አይ ቪ ኤድስ ትኩረት አልተሰጠውም ብሏል።

እንደ ጽህፈት ቤቱ መረጃ በኢትዮጵያችን በ2020 ብቻ 12ሺ 685 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 7179 ሴቶች ፣እንዲሁም 5506 ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተነግሯል።

በቫይረሱ ሕይወታቸው ካለፉት ውስጥ 16 በመቶው ህጻናት ናቸውም ተብሏል።

ኮሮና ቫይረስ፣ምርጫ እና ሌሎች ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ለኤች አይ ቪ ቫይረስ ትኩረት እንዳይሰጥ አድርጓል ያለው ጽ/ቤቱ ኤች አይ ቪ በደማቸው ከተገኘባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ 23 በመቶው የሚሆኑት እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑ እንደሆኑም ተገልጿል።

እንደ ጽህፈት ቤቱም ገለጻ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ 2 እጥፍ በኤች አይ ቪ እንደተያዙ ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
ሚያዝያ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.