አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ መመደቧ ለቀጠናው ካላት ትኩረት መሆኑን ኢትዮጵያ ገለፀች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ የሾመችው ልዩ መልእክተኛ ለአፍሪካ ቀንድ ካላት ትኩረት ነው የሚል እምነት አለን ብለዋል።

ይሁንእንጅ አዲሱ ተሿሚ ስለኢትዮጵያ ሰጥተዋል ስለተባለው መግለጫ ሀሳብ መስጠት እንደማይፈልጉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትናትናው ዕለት በምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ መሾማቸው ተነግሯል።

የምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ጄፍሪ ፌልተማን በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን አስታውቀዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ፖለቲካ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በትኩረት አሜሪካ እሰራለሁ ብላለች ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.