የአውሮፓ ህብረት አስትራዜኒካን ከሰሰ፡፡

የአውሮፓ ህብረት ሰኞ ዕለት በሕክምናው መስክ ግዙፍ በሆነው አስትራዜኔካ ላይ በኮሮና ቫይረስ ክትባት አቅርቦትን በማዘግየቱ በአህጉራችን አውሮፓ ለማስጀመር ያቀድነውን ጥረት አደናቅፎብናል በማለት መክሰሱን ተሰምቷል ፡፡

የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ እስቴፋን ዴ ኬርስማየር እንዳሉት ኮሚሽኑ ባለፈው አርብ በተሻሻለው የግዢ ስምምነት ጥሰት ላይ በመመስረት ኩባንያው አስትራዜኔካ ላይ ክስ መመስረታቸውን ተናግረዋል፡፡

ኩባንያው ክትባቱን በወቅቱ ማድረሱን የሚያረጋግጥ አስተማማኝ ስትራቴጂ ለማውጣት በሚያስችል ሁኔታ ላይ አልነበረም በዚህም በየኮንትራት ውሉ አልተከበረም ብለዋል፡፡

ለእኛ አስፈላጊ የሆነው ነገር እኛ የአውሮፓውያን ዜጎች በውሉ መሠረት ቃል የተገቡ የክትባት መጠኖችን በፍጥነት መድረሱን ማረጋገጥ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

አስትራዜኔካ ከአውሮፓ ኮሚሽን ጋር የቅድሚያ የግዢ ስምምነትን መፈፀሙን እና ኮሚሽኑ እስካሁን ውሉን ሙሉ ለሙሉ ያከበረ በመሆኑ ኩባያውን በፍርድ ቤት ልትጠይቅ መሆኙዋን ኤ.ኤፕ ዘግቧል፡፡

አስትራዜኔካ በአፕሪል መጨረሻ ወደ 50 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ክትባቶችን ወደ አውሮፓ ማድረስ ይገባ እንደነበር፣ ነገር ግን ይህ ብራሰልስ መድረስ ከነበረበት መጠን በጣም ያነሰ እደሆነ ተገልጿል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በዳዊት አስታጥቄ
ሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *